በጫኝና አውራጅ ማህበራት በተደረገው የዋጋ ተመን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በጫኝና አውራጅ ማህበራት በተደረገው የዋጋ ተመን ማሻሸያ፣ጥናት እና ትንተና ሰነድ ላይ የጋራ ውይይት ተካሄደ።

በጫኝና አውራጅ ማህበራት በተደረገው የዋጋ ተመን ማሻሸያ፣ጥናት እና ትንተና ሰነድ ላይ የጋራ ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በዛሬው ዕለት ከጫኝና አውራጅ ማህበራት እና ከነጋዴ ማህበራት ጋር በጫኝና አውራጅ ማህበራት በተደረገው የዋጋ ተመን ማሻሸያ፣ጥናት እና ትንተና ሰነድ ላይ የጋራ ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በከተማችን ላይ የጫኝና አውራጅ አደረጃጀት በመፈጠሩ ፣ በከተማው ውስጥ የነበሩ ዝርፊያዎች ፣ ንጥቂያዎች ፣ ህገወጥ ንግዶችና ሌሎችም መሠል ወንጀሎችን መቅረፍ ፣ በሚጭኑና በሚያስጭኑ መካከል ያለውን ችግር መፍታት መቻሉን ገልጸው፣ አንዳንድ የጫኝና አውራጅ አደረጃጀቶች እና ነጋዴዎች መካከል የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርሱ ድርጊቶችን መታገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ለመወያያ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የሰላም ሰራዊት የፀጥታ አደረጃጀቶችና ማህበራት ግንባታ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ር ሙልጌታ በጋሻው በገለጻቸውም በቢሮ የተደራጁ የጫኝና አውራጅ ማህበራት መመሪያን መሠረት በማድረግ ቀደም ሲል የወጣላቸው የዋጋ ተመን የወቅቱን ነባራዊ የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆንና ያልተካተቱ ዝርዝር ዋጋዎች በመኖራቸው ችግር ያለባቸውን አሰራሮች በመለየትና በጥናት የተደገፈ የዋጋ ማሻሸያ ማድረግ እና ማህበራቱን በተገቢው ሁኔታ እንዲደራጁ በማድረግ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመሥራት እንዲሁም የከተማችንን ሰላም በማስጠበቅ ወንጀሎችን በመከላከል ላይ አጋዥ ኃይል እንዲሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው ብለዋል።

በከተማው በወጣው እና ተግባራዊ በሆነው የጫኝና አውራጅ ማህበራት መመሪያ መሠረት ማህበራቱ በተጠናው የዋጋ ማሻሸያና በተካተቱ ዝርዝር ዕቃዎች መሠረት የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ ከፍ ማድረግ እንዲሆን የመጫኛና የማውረጃ ተመን አገልግሎት ሰጭውንም ሆነ አገልግሎት ተቀባዩን ያማከለና የወቅቱን የገበያ ዋጋ መሠረት ያደረገ እንዲሆን በማድረግ ህገ ወጥ ንግድን መቀነስ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ተጠቅሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙቀት ታረቀኝ እንደተናገሩት በመድረኩ የተሳተፉ የነጋዴ እና የጫኝና አውራጅ ማህበራት በጋራ ሆነው መወያየት ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሰው ሁለቱም ማህበራት በአንድ ስርዓትና ህግ የሚመራና ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጎ መስራት እንደሚገባ እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በማየት በጋራ በመስራት ህግ የማስከበር ስራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

በውይይቱም ወቅትም እንደተገለጸው ክ/ከተሞችና ወረዳዎች የጫኝና አውራጅ መመሪያ የዋጋ ተመን ዙሪያ ለሚመለከተው ሁሉ የሚደረግበት ሰፊ የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል ስራ መስራት እና አንዳንድ የጫኝና አውራጅ አደረጃጀቶች ላይ መካተት የሚገባቸው ሰዎች በጥናት ተለይተው የሚመለከታቸው ብቻ እንዲደራጁ ማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/.../e5702bda-a953-4926-8253...