የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና

በአገር በቀል በግጭት አያያዝና አፈታት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ዛሬም ቀጥሏል፡፡

ጥቅምት 08/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

***

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴትና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ በአገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ ጫኝና አውራጅ ማህበራት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናውም የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን እጅጉና ቡድን መሪዎች የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች አንዲሁም የጫኝና አውራጅ ማህበራት አባላት ተገኝተዋል።

ለግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀውን ሰነዱ ያቀረቡት የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ እንደተናገሩት የሰላምና የግጭት ምንነት፣ የግጭት መንሴዎች፣የባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ማለትም ሽምግልና ወይም ዕርቅ፤ድርድር፤ምክክር ትብብር.ወዘተ ርዕሶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኤሊያስ በማብራሪያቸው የጫኝና አውራጅ ማህበራት ካሁን ቀደም በሚሰጡት አገልግሎት በርካታ ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ አሳራሮችንና ተግባራትን ሲፈፀሙ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ጊዜ ህጋዊ አደረጃጀትን ተከትለው በመዋቀራቸውና በአባላቱ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ በቢሮው በመሰራቱ ከፀጥታ ስጋት ነፃ ሆነው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልፀው አሁን ያለውም አደረጃጀት ግጭትን አስቀድሞ በመለየትና በመከላከል ሰላማዊ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ አውድ መፍጠር ይኖርባቸዋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በማጠቃለያ ውይይቱ ላይ ተገኝተው ውይይቱን የመሩት የቢሮው የኃይማት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርነት አቶ ተመስገን እጅጉ በበኩላቸው የጫኝና አውራጅ ማህበራት አባላት በስራዎቻቸው አከባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶች ላይ፣ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ጊዜያቸውን ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን በመቆጠብ ሰላማዊ የሥራ አከባቢን መፍጠርና አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ቅምት 06/2017 ዓ.ም ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።