የአንድ ማዕከል ስምሪት የተለያዩ የፀጥታ አካላትን በቅንጅት በማሰማራት የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
የአንድ ማዕከል ስምሪት የተለያዩ የፀጥታ አካላትን በቅንጅት በማሰማራት የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
አቶ ጌታሁን አበራ
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማውን ሰላም በማረጋገጥ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባና ከተማዋ የስበት ማእከል እንድትሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።ይህን በውጤት የታጀበ ለማድረግም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ ጋር በጋራ በመሆን የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ እንዳሉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም የተረጋገጠው ህዝቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራት በመቻሉ ነው ብለው በዚህም ከተማችን የተለያዩ ኩነቶችን ያለምንም የፀጥታ ችግር ማከናወን ችላለች ብለዋል።
የቢሮው አማካሪ አክለውም የሰላም ሰራዊቱ ለመደበኛው የፀጥታ አካል የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልፀው ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋና ችረዋል አያይዘውም የአንድ መአከል የፀጥታ አሰራር የመረጃ ልውውጥን ለማፍጠን ፣ ለፀጥታ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ፣ ወንጀልን ለመከላከልና ህግን ለማስከበር አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
አቶ አህመድ ሀሰን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በስምሪት አሰጣጡ ላይ ተገኝተው እንዳሉት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ስጋት መከናወን የቻለው በህዝቡ ተሳትፎና የጋራ የቅንጅት ስራ መሆኑን ጠቁመው ያልተበረዘ ታሪክ ያላትን ሀገር ተሻጋሪነቷን ማስመስከር ተችሏል ብለው የከተማችን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የሰላም ሰራዊቱ ከመደኛው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ያለውን አኩሪ ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የአንድ ማእከል ስምሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ብሎም ወንጀልንና ወንጀሎችን በመቅጣጠር የህግ የበላይነትን የማስፈን ስራ በልዩ ትኩረትና በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/.../e5702bda-a953-4926-8253...