ህብረተሰቡን ግንባር ቀደም ተሳታፊ በማድረግ አስተማማኝ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ።
ህብረተሰቡን ግንባር ቀደም ተሳታፊ በማድረግ አስተማማኝ ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አጠቃላይ የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ የሰላም ባህል በመገንባትና ህብረተሰቡን ግንባር ቀደም ተሳታፊ በማድረግ ወንጀልንና ህገ-ወጥ ተግባራትን መከላከልና በዚህ ረገድ አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ ከፀጥታ ጥምር ሀይል ጋር የዉይይት መድረክ ተካሄደ።
በዉይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት ህገ-ወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ አጀንዳ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራዎች፣ ህገ-ወጥ ንግዶች እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ሊፈጥሩ የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ማድረግ እና የጋራ እርምጃ የመውሰድ አቅም በእጅጉ መጠናከር እንዳለበት አመላክተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀንጋቱ መሀመድ በበኩላቸዉ ክፍለ ከተማው የህዝቡን የሰላም ባለቤትነት የበለጠ በማጠናከር፣ ወንጀልን የመከላከል እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራን ተቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የክ/ከተማዉ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲስ ዘዉዴ መወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱ ወንጀልና ህገወጥነትን ከመቀነስ አንፃር ማህበረሰቡን በማሳተፍና ቆንጅታዊ አሰራር በማጠናከር አጠቃላይ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ መሆኑ በስፋት ተዳሷል።
የመድረኩ ተሳታፊወች በሰጡት ሀሳብ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ብሎም ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በእኔነት ስሜት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/.../e5702bda-a953-4926-8253...
See less