በበጀት አመቱ በ90 ቀናት እቅድ ላይ በማተኮር የ45 ቀናት ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ።
በበጀት አመቱ በ90 ቀናት እቅድ ላይ በማተኮር የ45 ቀናት ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ።
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም(PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018/19 በጀት አመት በ90 ቀናት እቅድ ዙሪያ ባለፉት 45 ቀናት ዉስጥ የተተገበሩ ተግባራት ዝርዝር ሪፖርት ከማእከል እስከ ወረዳ ያሉ የዘርፉ አመራሮች በተገኙበት በሰነድ መልክ ቀርቦ ዉይይት ተካሄዶበታል።
መድረኩን የመሩት የቢሮው ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፤ ባለፉት ቀናት የፀጥታና የደህንነት ስራዎች የተመራበት አግባብ አመርቂ መሆኑን አንስተው ከተማዋ ላይ የሚታየው ሰላማዊ ሂደት በቀጣይ ቀናት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የፀጥታ ስምሪት አሰጣጥን በማጠናከር በሁሉም ክ/ከተሞች በሙሉ አቅም መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ኃላፊዋ አክለውም ለመደበኛ የፀጥታ አካላት አጋዥ በመሆን የአካባቢን ሰላም የማስጠበቅ ሂደት ላይ የተደራጁ የሰላም ሠራዊት መረጃን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሲስተም ውስጥ እንዲገባ መደረጉንና ስምሪቱም በሦስት ፈረቃ እየተከናወነ ያለበት ሂደትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
ከዚሁ ጎን ለጎን ወቅቱ ክረምት መሆኑን በማንሳት፣ የወንጀል መከላከል ስራ በልዩ ትኩረት ማከናወን ከዚሁ ጎን ለጎን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች በየክፍለ ከተማው በእኩል አፈፃፀም ተግባሪ ማድረግ ይጠበቃል ብለው የሚስተዋሉ አዝማሚያዎችን መሠረት በማድረግ ሰላማዊ ከተማን ለማስቀጠል በንቃት መስራትና የተለየ ስልት በመቀየስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊና የጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር የ90 ቀናት ዕቅድ የ45 ቀናት አፈፃፀም ሪፖርት በአራቱም የቢሮዉ ዘርፎች የተከናወኑ አበይት ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በታቀደዉ እቅድ መሠረት መጠነ ሰፊ የሠላምና ደህንነት ፣ የዲጂታል ሰላም ግንባታ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ስራዎች ሲሰራ መቆየቱና የተስተዋሉ ክፍተቶች በዝርዝር አቅርበዋል ።
በመጨረሻም ከመድረኩ ተሳታፊዎች ዕቅድን ለማሳካት አቅም አሟጦ ከመጠቀም አንፃር ውስንነቶች መኖራቸው ፣ ለወንጀል መንስኤ የሆኑ ቦታዎችን የመለየትና የቅድመ መከላከል ስራ ማጠናከር ፣ የሰላም ሰራዊት መረጃን ማጥራትና ማደራጀት ፣ የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያሉትን ሂደቶች ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራትና መሰል ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተነስቶ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የተቋም ግንባታ ስራን ማጠናከርና የመስሪያ ቦታን ምቹ ማድረግ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማጠናከርና በመአከል የለሙትን ወደ ስራ መግባት ፣ የሰላም ሰራዊት ስምሪትን በሶስት ሽፍት መስጠትን አጠናክሮ ማስቀጠልና መረጃውን በሲስተም ማደራጀት ፣ የማህበረሰብ ተኮር ውይይትን ማጠናከር፣ የሰላም እሴት ግንባታ ፣ የሀይማኖት ጉባኤ ስራዎችን ማጠናከር ፣ ለፀጥታ አስጊ የሆኑ ጉዳዮችን መለየትና የወንጀል መንስኤዎችን ማጥፋት ፣ የኢኮኖሚ አሻጥርን መቆጣጠር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/.../e5702bda-a953-4926-8253...