የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ አስተዳደሮች በ2018 በጀት ዓመት በፀጥታና በህግ ማስከበር ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት የጋራ የቅንጅት ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ የአፈፃፀም አቅጣጫ አስቀመጡ።
የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ አስተዳደሮች በ2018 በጀት ዓመት በፀጥታና በህግ ማስከበር ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት የጋራ የቅንጅት ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ የአፈፃፀም አቅጣጫ አስቀመጡ።
የሁለቱ ከተሞች የጋራ የቅንጅት ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ በተገባው መሰረት ውጤታማ የፀጥታና የወንጀል መከላከል ስራዎች በመስራት የህግ ማስከበር ላይ ውጤታማ ስራ የተሰራ መሆኑንና በዚህም በሀለቱም ከተሞች ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ መቻሉ በውይይት መድረኩ ተመላክቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መድረኩን ሲከፍቱ እንዳሉት ባለፈው በጀት ዓመት በሁለቱ ከተሞች ቅንጅት የተገኘው ውጤት የሚያስመሰግንና የህብረተሰቡን ሰላም ያረጋገጠ መሆኑን ገልፀዋል።
በ2018 አፈፃፀም የተገኘውን ውጤት ለቀጣይ ስንቅ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በልዩ ትኩረት መስራትና የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባና የከተሞቹን አሁናዊ የፀጥታ አዝማሚያን የሚረዳ ሀይል እንዲኖር የሰላም ሰራዊቱንና ጋቸና ሲርና ህዝባዊ አደረጃጀቶችን ከመደበኛው የፀጥታ ሀይል ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ማድሰግ በተለያየ ሁኔታ መደገፍና ብቁ ማድረግ፣ የንግድ ቁጥጥር ስርዓትን ማሻሻልና የምርት አቅርቦት ያለአግባብ የሚያከማቹ ነጋዴዎች ላይ አሰራርን መሰረት ያደረገ እርምጃ መውሰድ ፣ የሁሉቱ ከተሞች ትስስርን የሚያጋምድና የህዝብ ለህዝብ ቁርኝት በሚያጠናክር መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
የወንጀል ምጣኔን ከአሁኑ በበለጠ ለመቀነስ ህዝቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ማጠናከር፣ የፀረ ሰላም ሀይሎችን ለመመከት በቅንጅት መስራት ፣ የህገወጥ የንግድ ስርአትንና ምርት ያለአግባብ የሚከዝኑ ነጋዴዎች ላይ አሰራርን መሰረት ያደረገ እርምጃ መውሰድና ወደ ህጋዊ ስርአት እንዲገቡ ማድረግ ፣ የሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት መስራትና በ2018 የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የፊታችን የማሚከናወኑ የአደባባይ በአላት ተደማሪ አቅም እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ ቢሮ ኃላፊዋ አሳስበዋል።
አቶ ጉዮ ገልገሎ የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እንደገለፁት የሁለቱ ከተሞች በጋራና በቅንጅት በመሰራቱ ባለፈው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራዎችን በስኬት የታጀበ እንዲሆን ማስቻሉን አንስተው አሁንም የከተሞቹ ቅንጅትና ጥምረት ለህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ መግባትና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረትና የበለጠ ተቀራርቦ በየጊዜው ተግባራትን እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ለ2019 በጀት ዓመት በሁለቱ ከተሞች መካከል የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር፣ የጋራ ኦፕሬሽኖችን ማስፋት፣ የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፣ የህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ እና ዘላቂ የሰላምና ፀጥታ ስርዓት ለመገንባት በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል።
ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157