የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ አስተዳ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር በፀጥታ ፣ በወንጀል መከላከልና የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ በጋራ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈራረሙ

የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ  አስተዳደር በፀጥታ ፣  በወንጀል መከላከልና  የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ በጋራ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች  ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በተለየ መልኩ ጥረት ማድረግና ማስጠበቅ ፣ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቶችን በሎጀስቲክና በተለያዩ ስልጠናዎች መደገፍ ፣ የድጋፍና ክትትል ስራን ማጠናከር  ፣ ጨለማን ተገን አድርጎ የሚሰሩ ወንጀልንና  የስጋት ቦታዎችን በመለየት ህብረተሰቡ መረጃ እንዲሰጥና ለፀጥታ ሀይሉ አቅም እንዲሆን ማስቻል  ፣ የፀረ ሽብርተኞችን አሸንቅስቃሴዎችን ተከታትሎ ማጥፋት፣ማህበረሰቡ ከአደጋ ስጋቶች እራሳቸውን እንዲጠብቁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ላይ ትኩረት ያደረገ የጋራ የውል ስምምነት የከተሞቹ  ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተፈራርመዋል።

ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157