የከተማችንን ሰላም ለማስቀጠል የሰለም ሰራዊት አባላት በቅንጅትና በመናበብ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።
የከተማችንን ሰላም ለማስቀጠል የሰለም ሰራዊት አባላት በቅንጅትና በመናበብ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራን በማጠናከር የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠና የህግ የበላይነትን እያስከበረ ሲሆን ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ዛሬ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የአንድ ማእከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጥቷል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስምሪት አሰጣጡ ላይ ተገኝተው እንዳሉት አሁን ላይ ከተማችን ላይ ያለውን ሰላማዊ እንቅስቃሴና ልማት ለማስቀጠል ህዝባዊ አደረጃጀቱ ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለበትን ሂደት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በከተማችን እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከሰላም ሰራዊቱና ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቆም የአካባቢን ሰላም ማስጠበቅና አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ጥቆማ በመስጠት ተባባሪ መሆን እንዳለበት ኃላፊው ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካል ጋር በጋራ በመሆን፣ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ህግን መሠረት በማድረግ አሁን ላይ የከተማችን ሰላም አፅንቶ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ በስምሪቱ በመገኘት እንደተናገሩት ሰላም ሰራዊት አባላት ለሀገራቹ ያለአንዳች ክፍያ ሰላሟን በማስጠበቅ የምትገኙ፣ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ሰላሟን በማስጠበቅ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን እየሰሠሩ እንደሚገኙ ገልጸው፣አሁን ሀገራችን ምክክር እያረገች እንደሆነና በአከባቢያቹ ፀጉረ ለውጦችን በመከታተል ዜጎች በሰላም ወጥቶ እንዲገቡ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ አየለ ተስፋዬ የለሚ ኩራ ክ/ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት የሰላም ሰራዊቱ ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በክ/ከተማው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር አስችሏል ብለው ይህን ማጠናከርና የሰላም ሰራዊቱ መረጃን በመስጠትና የአከባቢያቸውን ሰላም ማስጠበቅ ላይ የተጠናከረ ስራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በስምሪት አሰጣጡ ላይ እንደተመላከተው በከተማችን ሰላምና ፀጥታን ማጠናከር፣ የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ህግን ማስከበር እና ዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በሰላም እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
የከተማ ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ፣ የፀጥታ አካላትና የሰላም ሰራዊት በስምሪቱ ላይ ተገኝተዋል።
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157