ቢሮው በቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ዙሪያ በ90 ቀናት የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ።
ቢሮው በቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ዙሪያ በ90 ቀናት የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ።
ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በ90 ቀናት የተያዙ የቴክኖሎጂዎች ማልማትና የለሙ ሲስተሞችን ወደ ተግባር ከማስገባት አንጻር የነበረውን አጠቃላይ ሂደት ገመገመ።
የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው በመሩት በዚህ የዉይይት መድረክ ላይ የማዕከልና የሁሉም ክፍለ ከተሞች "ፎካል ፐርሰኖች" ተገኙ ሲሆን፤ በየክፍለ ከተማቸው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የመረጃ ፍሰት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበዋል።
በመድረኩ በቢሮው የ IT ባለሙያ ወ/ሪት ጸሐይነሽ ብርሃኑ አማካኝነት በበጀት ዓመቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፣ የለሙ ሲስተሞችና ያጋጠሙ ሁኔታዎች በሰነድ መልክ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
መድረኩን የመሩት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው በንግግራቸው የከተማዉን ሰላምና ጸጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅና የወንጀል ስጋቶችን በቅድመ-መከላከል ለማስቀረት የቴክኖሎጂ ትግበራ ወሳኝ እና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው ብለዋል።
አማካሪዉ አክለውም የለሙ የቴክኖሎጂ አሰራሮች የሰላምና ጸጥታ መረጃዎችን በጥራትና በፍጥነት ለመለዋወጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም የለሙ ቴክኖሎጂዎችን በየክፍለ ከተማው የሚገኙ መዋቅሮች በማእከል ደረጃ የተዘረጉትን የቴክኖሎጂ ሲስተሞች በሙሉ አቅማቸው በመጠቀም የመረጃ ፍሰቱን ይበልጥ የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚገባቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157