ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን የመብራት ማስበራት፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ማዕከላት ፈጠራ ኮሚቴ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የትግበራ ሂደትን ተዘዋውሮ ጎበኘ።
ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን የመብራት ማስበራት፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ማዕከላት ፈጠራ ኮሚቴ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የትግበራ ሂደትን ተዘዋውሮ ጎበኘ።
*
ነሃሴ 02/2018 ዓ.ም(PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን 7/24 እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለቅሚያና ንጥቂያ መነሻ የሆኑ ህብረተሰቡን ለወንጀል የሚዳርጉ የዉስጥ ለዉስጥና የመንገድ ዳር ጨለማ ስፍራዎችን ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲወስድ በማድረግ ስፍራዎቹ ሙሉ በሙሉ ብርሃናማ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተር መፍጠር ቀዳሚ ተግባር አድርጎ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል። ይህን ተግባር የሚመራው ኮሚቴም ባሳለፍናቸዉ ጊዜያቶች የተለያዩ የሚመለከታቸው ዘርፎች ከማእከል አስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችን ባሳተፈ መልኩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በምሽት በመዘዋወር የስራውን ሂደት ሲገመግምና ማሻሻያ የሚፈልጉ አሰራሮችን ማስተካከያ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ፤ ይህን ተጠናክሮ የቀጠለው ተግባር በዛሬዉ እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ከዚህ ቀደም በምሽት ለመንቀሳቀስ ስጋት የሆኑ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ብርሃናማ የሆኑ ስፍራዎችንና የሲሲቲቪ ካሜራዎች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የመስክ ምልከታ አድርጓል።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊና በኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የተመራዉ ግብረሀይል በክፍለ ከተማዉ ያሉ ወረዳዎችን የዉስጥ ለዉስጥና የመንገድ ዳር መብራቶችንና የሞዴል ፖሊስ ሴንተሮችን ያሉበትን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፤
ክብርት ሀላፊዋ የመስክ ምልከታዉን ለማስጀመር ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት፤በተያዘዉ በጀት አመት በጸጥታና ደህንነት ስራዎች መሻሻሎች በመምጣቱ አስተማማኝ ሰላም በከተማዋ እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉን ጠቁመዉ ፣ የመብራት ማስበራት መርሃግብሩ ጨለማን በብርሃን በመተካት ወንጀልንና ወንጀለኞችን በመቀነስ የህብረተሰቡን በሰላም ወጥቶ መግባት እንዲችል ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።
ከተማችን አዲስ አበባ የብሔር ብሔረሰቦች የአንድነት መገለጫ እንደ መሆኗ በርካታ የአደባባይ ላይ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ሁነቶች የሚካሄድባት እንደመሆኗ ወንጀልን በመቀነስ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ማስፈን ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ያነሱት ኃላፊዋ ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ እየሆነች በመምጣቷ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሰላም፣ጸጥታና የደህንነት ስራን ማጠናከር ፣ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት ለወንጀል መንስኤ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የሚከሰቱ ወንጀሎችን የመቀነስ ስራ ተሰርቷል ሲሉም ገልጸዋል።
ሀላፊዋ አክለዉም በበጀት አመቱ 47 በመቶ የወንጀል ቅነሳ መደረጉን ያነሱ ሲሆን በየ ብሎኩ በካሜራ የታገዘ ስራ በመስራት በከተማዉ በሰላምና ደህንነት ስራ የመጡ ዉጤቶችን የተሻለና የተጠናከረ በማድረግ ከፊታችን ያሉ ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆኑ የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ የመለየት ስራ መስራት እንደሚገባ አንስተዉ ህብረተሰቡም ከዚህ ቀደም ያሳየዉን የሰላም ባለቤትነት ከመላው ጸጥታ መዋቅሮች ጋር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ሀሰን በበኩላቸው በከተማዉ እየተደረገ ያለዉን የወንጀል መከላከልና ከተማዋን የሰላም ፈርጥ ለማድረግ በተጀመረዉ ሂደት የሰላም ተምሳሌትና የብልጽግና መገለጫ በሆነችዉ ላፍቶ ላይ ህብረተሰቡ ያለ ምንም ስጋት እንዲንቀሳቀስ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን አዉስተዉ ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።
በምልከታዉ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና ኮሚሽነር ይመር ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጨምሮ የከተማ ፣ የ11ዱም ክ/ከተማና የ119ኙም ወረዳ
የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና የደንብ ማስከበር አመራሮች፣ ኦፊሰሮችና የሰላም ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157