የቅድመ ወንጀል መከላከልና የፀጥታና የደህንነት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቅድመ ወንጀል መከላከልና የፀጥታና የደህንነት ስራ በትኩረት በመሰራቱ በከተማው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉ ተገለፀ።

የቅድመ ወንጀል መከላከልና  የፀጥታና የደህንነት ስራ በትኩረት በመሰራቱ በከተማው  ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተር ፈጠራ ኮሚቴ የአጭር ጊዜ አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የፀጥታና የወንጀል መከላከል  ስራ የነዋሪዎች የዘወትር እንቅስቃሴ ላይ መሰረት ያደረገ እንደመሆኑ  ኮሚቴው  የከተማው ነዋሪ ያለምንም የፀጥታ ስጋት  ወጥተው መግባት እንዲችሉ  የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር  በመቀናጀት የውስጥ ለውስጥ መብራት ማስበራት ፣  የፖሊስ ሴንተሮችን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ    የሲሲቲቪ ካሜራ በመግጠም በትኩረት እየሰራ መሆኑንና በዚህም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት መቻሉን ገምግሟል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የኮሚቴው ሰብሳቢ በግምገማ መድረኩ ላይ እንዳሉት አሁን ላይ በሁሉም ክ/ከተሞች እየተሰራበት ያለው የውስጥ ለውስጥ መብራትና የሲሲቲቪ ካሜራ የትግበራ ሂደት ውጤት ያመጣ መሆኑን ገልፀው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ  ጥገና የሚያስፈልጋቸውን የመብራት መስመሮችን  በየጊዜው እንዲጠገኑ ማድረግ ሌሎች መሰል ተግባሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ አያይዘውም ከተማዋ በፈጣን የዕድገት ግስጋሴ ላይ እንደመሆኗ  ሰላሟ የተረጋገጠባት እንድትሆን የተጀመሩና አሁን ላይ ውጤት እያሳዩ ያሉ  የቅድመ ወንጀል መከላከልና  የፀጥታና የደህንነት ስራን በማጠናከር  የሲሲቲቪ ካሜራ  24 ሰአት እንዲሰራ ማድረግና ጥብቅ የክትትል ስራ በመስራት ያለውን ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበው የመሰረተ ልማት ስርቆት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

አቶ አህመድ ሀሰን የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፀጥታ ስራ ጊዜ የማይሰጥ እንደመሆኑ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የቅድመ ወንጀል መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግና ይህም ዜጎች ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ያስችላል ብለው ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁን ላይ ያለውን የአፈፃፀም ውጤታማነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅትና በመናበብ መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር  የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር  ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን  ዘርፍ ኃላፊ   ኮሚቴው ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ  የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተሮችን የመፍጠር ስራ በሁሉም ክ/ከተሞች ያለውን የአፈፃፀም ደረጃ በዝርዝር አብራርተዋል። ኃላፊው አክለውም  በአጭር ጊዜ ኮሚቴው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀው የታዩ ክፍተቶችና የማስተካከያ አካሄድ አስቀምጠዋል።

በግምገማው ላይ  የነበሩ  ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶች ላይ አስቸኳይ እርምት በመውሰድ በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።

ነሀሴ 2/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157