የከተማው ነዋሪዎች ስልጠና

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የከተማው ነዋሪዎች ስልጠና

ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

ጥቅምት 13/ 2017 ዓ.ም

(አዲስ አበባ)

***

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴትና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ በአገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ ነዋሪዎች ስልጠና ሰጥተዋል።

ለግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ አዲስ ዓለም ዘነበ የሰላምና የግጭት ምንነት፣ የግጭት መንሴዎች፣የባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ማለትም ሽምግልና ወይም ዕርቅ፤ድርድር፤ምክክር ትብብር.ወዘተ ርዕሶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ አዲስ ዓለም በማብራሪያቸውም ፍትሃዊነት በሌለበት አዎንታዊ ሰላም አለ ማለት እንደማይቻል ጠቁመው የመልካም አስተዳደር እጦት ወደ ግጭት ስለሚያመራ በየትኛውም መስክ ፍትሃዊ አሰራርን ማስፈን ይገባል ካሉ በኃላ ግጭት ተፈጥሮአዊ ስለሆነ መፋታትና ማስተዳደር እንጂ ጨርሶ ማስወገድ አይቻልም በማለት ገልፀዋል።

መድረኩን የመሩት የዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ተመስገን እጅጉ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በባህላዊ ዘዴዎች ግጭትን መፍተት በአገራችን ቀድሞ የነበረ እና አሁንም ያለ ዕሴታችን በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ተመስገን አክለውም የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሚትኖሩበት አከባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶች ላይ፣ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅመን ይርቅ በመውረድ የአገራችን ዘላቂ ሰላም ለማስቀጠል ሁላችን ድርሻችንን እንውጣ ብለዋል።