የ1ኛ ሩብ ዓመት ግምገማ

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ1ኛ ሩብ ዓመት ግምገማ

የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድን ገመገመ።

ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

* *

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በጋራ አብረው ከተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድን ገምግሞአል::

የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በ ዚህን ወቅት እንደተናገሩት ቢሮው 11 ሺህ ወጣት የሰላም ሰራዊት አባአላት አሰልጥኖ ከነባር የሰላም ሰራዊት ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ፣ በከተማዋ የጫኝ እና አዉራጆችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግረዋል ።

ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የህብረሰብ ክፍሎችን በሰላም ዙሪያ ማወያየቱ በሩብ አመቱ ከነበሩ አንኳር ተግባራት መካከል መሆናቸዉን አንስተዋል ።

በተለይ ህብረተሰቡን ያማከሉ በርካታ ተግባራት በመተግበራቸዉ የአዲስ አበባን ሰላም ማጠናከር ችሏልም ብለዋል ።

የበጀት አመቱ ሩብ አመት በከተማዋ በርካታ የአደባባይ በአላትንና አለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን ያለምንም የጸጥታ ችግር ያከናወነችበት እንደነበርም አንስተዋል ምክትል ቢሮ ሃላፊዉ ።

ለዚህ ስኬት የህብረተሰብ አደረጃጀቶች የአንበሳዉን ድርሻ ተወጥተዋል ብለዋል ።