ፖሊስ ኮሚሽን ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የ ስ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ፖሊስ ኮሚሽን ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የ ስራ ኃላፊዎችና አባላት ጋር የተደረጌ ውይይት

በየደረጃዉ ከሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የ ስራ ኃላፊዎችና አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ ።

ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ

በየደረጃዉ ከሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የ ስራ ኃላፊዎችና አባላት ጋር ውይይት ተደርጎዋል::

በ2017ዓ.ም በተያዘው ዕቅድ መሰረት ለአስራ አንድ ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብና የመስክ ወታደራዊ ስልጠና በአንደኛ ሩብ ዓመት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ወቅት የነበሩ ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ አቶ አብርሃም እንግዳወርቅ የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ማብራሪያ ተሰጥቶዋል ።

የሰላም ሰራዊቱ ስልጠና አቅምን የፈጠረ እንደሆነ ሁሉ የስምሪት ስራውን አጠና ክሮ በማስቀጠል የሚታዩ አንዳንድ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ ዕቅድና ጥናት ሀላፊ ም/ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ ገልጸዋል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደገለፁት የሰላም ዋስትናን ለማረጋገጥ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ሀይሉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም በየግዜው ህብረተሰቡን በየአካባቢው በማወያየት የሰላም ባለቤት በማድረግና አጋዥ እንዲሆኑ በማስቻል ወንጀሎችን ለ መቀነስ የሚደረገው ጥረትን በማድነቅ አምስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።