የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ሪፖርት ለይ የተደ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ሪፖርት ለይ የተደረጌ ውይይት

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ሪፖርት ለይ ውይይት አካሄዷል።

ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

(አዲስ አበባ)

***

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከ ሚገኙ ፎካል ፐርሰን ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ወረታ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚከሰተው የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ባለመከተል ስለሆነ በሙያ፣ አፈጻጸምና በድሲፕሊን ተጠያቂነት ሊ ሰማን ይገባል ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ ወረታ አክለውም የህግ ማ አቀፍ የሌላቸው ችግሮች እና በአንድ ተቋም ብቻ ሊፈቱ የማይችሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመወያየት ችግሩን መፍታት እንደሚገባ ገልፀው ፍትሃዊነትና ሳይኖር መልካም አስተዳደር ሊኖር አይችልም ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ሲሆኑ፦

ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ያጋጠሙት ችግሮች፣ የተሰጡ መፍትሔዎች....ወዘተ አብራርተዋል።

አቶ ገብሬ አክለዉም ግልጽነት በመፍጠር የችግሮች መንስኤ መጣራት እና ቅሬታ አፈታት በስታንዳርድ መፍታት እንደሚገባ በመግለፅ በተቋማችን ሌብነትና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር መከታተል አለብን ብለዋል።