ቢሮው ፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።
ለከተማችን ሰላም በጥፍራችን ቆመን እንሰራለን!
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር
• ቢሮው ፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።
ጥቅምት 18/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አስተባባሪ፣ዳይሬክተሮች፣
ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንድሁም ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አመራሮች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል።
መድረኩ ላይ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው ሲሆኑ፦ በሪፖርቱ በሩብ አመቱ በጥንካሬ፣ በድክመቶች፣ እና ያጋጠሙት ችግሮች..ወዘተ በዝርዝር አብራርተዋል።
ከጥንካሬዎች መካከል፡- ወንጀልን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ወንጀል እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ እና ሃይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው ማለፋቸው ቅንጅታዊ ስራዎች ስምሪትና ክትትል ተጠቃሸ ሲሆኑ የሰው ሃይልና የግብዓቶች እጥረት ደግሞ ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
መድረኩን የመሩት የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተሰፋዬ ደንድር እና የአዲስ አበባ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በአላት በሰላም ተከብረው ማለፋቸው በፀጥታ ኃሎች ጥምረትና በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ስለሆነ አመስግነው ይህ ሁሉ ውጤቶች የተገኘው ቅንጅታዊ አሰራርን ተከትለን በቅንጅት በማቀዳችንና በመሰማራታችን ስለሆነ አሁንም ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ይኸው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
አቶ ተስፈዬ አክለውም ፀረ ሰላም ኃይሎች በተናጥል፤በግልፅም ሆና በህቡዕ በመደራጀት ወንጀል ከመስራት እንደማይቦዝኑ እናውቃለን፡፡ይህም በመሆኑ እኛም ለአገራችን ሰላም በጥፍራችን ቆመን ሌት ተቀን እንሰራለን ብለዋል።
በመጨረሻም የፅንፈኛ ሃይል እንቅስቃሴ፣የደረቅ ወንጀል፤ በመኪና የታጀበ ንጥቂያ እንዳለና አዝማሚያዎችም ይህንን ስለሚያሳዩ በደንብ መከታተል፣ የሴትኛ አዳሪዎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች አከባቢ ትኩረት ማድረግ ፣ ትምህርት ቤት አከባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶችና የቡድን ፀብ በመሳሰሉት ላይ በንቃት መሰራት እንደሚገባ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።