በ2017 ዓ.ም በአንደኛ ሩብ ዓመት ውስጥ የተሰሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹ ሰላም የሰፈነባት ከተማ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ።
• አቶ ሚደቅሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ።
ጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
******
ም/ቢሮ ኃላፊው ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ የማህበረሰብ ክፋል ተወካዮች ጋር ምክክር ለማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው ።
በምክክር መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊዎች አማካሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በ2017 ዓ.ም በአንደኛ ሩብ ዓመት ውስጥ የተሰሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች በጥንካሬ፤በክፍተትና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ለመወያያ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ማብራሪያ የሠጡት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ሲሆኑ ባለፈዉ ሩብ ዓመት ውስጥ ቢሮው የጸጥታ ስጋት የሆኑ አካባቢዎችን የመለየት፤ በጫኝና አውራጅ ፤በባጃጅ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በንግዱም ዘርፍ የዋጋ ተመን በማናር የሚሰሩ ህገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል ከተሰሩት ስራዎች ጥቂቶቹ መሆናቸውን በአጠቃላይ የፀጥታ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በጥምረት ሀያ አራት ሰዓት በመስራታቸው ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ፤ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲዉሉ ማድረግ መቻሉን ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል።
በከተማው ውስጥ በየጊዜው ህብረተሰቡን በማወያየት የቢሮውን አግልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ጭምር በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ተችሏል ያሉት አቶ ሚደቅሳ ከበደ የቢሮው ም/ሀላፊ ሲሆኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹ ሰላም የሰፈነባት ከተማ የማድረግ ስራ ተሰርቷልብለዋል። ።
ም/ቢሮ ኃላፊው አክለውም የመልካም አስተዳደር እጦት የጸጥታ ስጋት እንዳይሆን ቢሮው በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ጭምር በመጠቆም ሰላም ከግለሰብ አልፎ ሀገርን ስለሚጠቅም አሁንም ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት ይገባልም ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲሁም ለጸጥታው ስራ አስጊ የሆኑ አካባቢዎች ላይ አሁንም እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማስገንዘብ የጸጥታ ስራ ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚሰራ ስላልሆነ አሁንም በባለቤትነት አብሮ በመስራት የከተማውን ሰላም ማስጠበቅ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡