ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የከተማው ሴት ማህበር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የከተማው ሴት ማህበር ተወካዮች ስልጠና

ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የከተማው ሴት ማህበር ተወካዮች ስልጠና ተሰጠ ።

ጥቅምት 20/ 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በአገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የከተማው ሴት ማህበር ተወካዮች ስልጠና ተሰጥቷል።

የሥልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ አዲስ ዓለም ዘነበ በከተማች ዘላቂ ሰላም ለማምጣት አገር በቀል ወይንም ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፤የሰላምና የግጭት ምንነት፣ መንስኤዎች ፣የባህላዊ የግጭት አፈታት ማለትም ሽምግልና ዕርቅ፣ድርድር፣

ይቅርታ እና ምክክር በሚሉ ርዕሶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ አዲስ ዓለም አያይዘውም የኢ-ፍትሃዊነት አሰራሮች ለግጭት መንስኤ ስለሚሆኑ ሁሉም ሰው ፍትሃዊ መሆን ይገባዋል፡፡ፍትሃዊነት በሌለበት አዎንታዊ ሰላም ሊኖር ስለማይችል በማንኛውም ጊዜ ፍትሃዊ አሰራርን ማስፈን ይገባል፡፡ ግጭት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ ጨርሶ ማስወገድ ባይቻልም ለግጭት መንስኤ የሆኑ ሁኔታዎችን በማስወገድ ዘላቂ ሰላም መምጣት ይቻላልም ብለዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደተናገሩት የአዲስ አበባን ሰላም መስፈን እኛ እንደምንፈልግ ሁሉ ሌሎች ደግሞ ሰላሟን ሊያደፈርሱ የሚተጉ አካላት እንዳሉ ተገንዝባችሁ በእኔነት መንፈስ ለከተማችን ሰላም ድርሻችሁን መወጣት ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡