ከሕዝብ ቅጥር ጥበቃዎችና ከግል የጥበቃ ኤጀንሲ አመራሮች ጋር የተደረገ ውይይት።
በከተማው ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና ወንጀልን ለመቀነስ ከሕዝብ ቅጥር ጥበቃዎችና ከግል የጥበቃ ኤጀንሲ አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ ።
ጥቅምት 21/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
** ** **
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ በከተማው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ወንጀልን ለመቀነስ ከቅጥር ጥበቃዎችና ከኤጀንሲ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል ።
ለውይይቱ መነሻ የሆነውን ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው ሲሆኑ የጥበቃው ስራ የሚሰራው ከህብረተሰቡ ከተመለመሉ ነዋሪዎች በመሆኑ የሚተዳደሩበት ህግና ደንብን በጠበቀ መልኩ በመስራት ማገልገል እንደሚገባቸው ጠቁመው በአሁን ወቅት በከተማዋ ላይ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች እየተከሰቱ ቢሆንም የሕዝብ ቅጥር ጥበቃ ሠራተኞች ህብረተሰቡ የጣለባቸውን ሀላፊነት ከመወጣት አንጻር ከጸጥታ ሀይሎችና ከሰላም ሠራዊት አባላት ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ ወንጀሎችን በመከላከል፣
በመቆጣጠርና ወንጀለኞችን አሳልፎም በመስጠት የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
በአፈፃፀም ረገድ አንዳንድ የሚታዩ ተገቢ ያልሆኑ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም አገልግሎቱ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ኮማንደር ሙሉጌታ በሰነዳቸው አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ጥቂት ሀይሎች ሰላምን ለማደፍረስ የተለያየ አፍራሽ የፖለቲካ አጀንዳዎችን በማንገብ የከተማውን ሰላም ለማደፍረስ የሚተጉ አካላትን ሴራ ለማክሸፍ ህብረተሰቡ ዋጋ እየከፈለ ነው ካሉ በኋላ አሁንም ህገ ወጥ ድርጊቶችን በመከታተል መከላከልና ለከተማችን ዘላቂ ሰላም መትጋት ይኖርበታል ሲሉ ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ም/ኮምሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በከተማው ውስጥ ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ብሎም የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፣
ሁሉንም ስራ በቅደም ተከተል ለማስኬድ የሰላም መጠበቅ ይኖርበታል፣ ሁሉም በየደረጃው የራሱንና የህብረሰቡን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ተግቶ መሥራት አለበት በማለት ተናግረዋል ።
በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አይ ኪባሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ም/ኮምሽነር፣
የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ሀላፊዎችና የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል