የቀጠለ ዜና

image description
- recent news   

የቀጠለ ዜና

 

"ግጭትን መከላከል፤ ማስተዳደርና ሰላምን መገንባት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ዋለ 

           ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም 

                 አዲስ አበባ

                  ******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች"ግጭትን መከላከል፤ማስተዳደርና ሰላምን መገን
ባት"በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ  ዉሏል 

ስልጠናውም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በአራዳ ክ/ከተማ የህዝብ መሰብሰብያ አዳራሽ ውስጥ ለአዲስ አበባ ሴቶች ማ ህበር አባላት የተሰጠ ሲሆን በስልጠና መድረኩ ላይም የቢሮዉ ም/ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ፣የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እናት ዓለም እንዳለ እንዲሁም  ም/ል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አፀደ ሀበነ ተገኝተዋል ::

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮቹን በንግግር የከፈቱት አቶ ሚደክሳ ከበደ የቢሮው ም/ል ኃላፊ ሲሆኑ በተለይ ሴቶች የከተማችንን ሰላም ለማፅናት በሰላም ሠራዊት አደረጃጀት ውስጥ በመካተት ጭለማ ፣ፀሐይ፣ብርድ ሳይበግራችሁ ለከፈላችሁት  መስዋ
ዕትነት ምስጋና አቅርባለሁ ብለዋል።
ም/ልቢሮ ኃላፊ አክለውም እናንተ የሰላም ትርጉም የገባችሁ ሴት እህቶች እናቶች በየቤታችሁ ካለባችሁ ተደራራቢ የቤተሰብ ኃላፊነቶች በተጨማሪ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የከተማችንን ሰላም እንዳስቀጠላችሁ ሁሉ አሁንም ትኩረትና ትጋታችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ ብለዋል።

በከሰዓት ክፍለ ጊዜ ደግሞ ለሰላም ም ክር ቤት አባላትና ለጥታ ኮሚቴ አባላት ሰጥቷል::

ለውይይቱ መነሻ የሆነውን ሰነድ በአቶ አብረሃም እንግዳወርቅ የቢሮው የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ተወካይና
በአቶ ልቅናው ታሪኩ ቡድን መሪ ቀርቦ ዉ ይይት የተደረገ ሲሆን በሰነዱም ሰላም የሚጀምረው ከራስ እንደሆነ፣ግጭት ተፈጥሯዊ መሆኑን በመረዳት ጨርሰን ልናስወግደው እንኳን ባንችል ልንከላከ
ልና ልንቀንሰው እንችላለን ፡፡

 በመነጋገርና በመከባበር መንፈስ የግጭት መንስኤዎችንና ችግሮችን  መፍታት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ 

ባለመግባባት ውስጥ በሚፈጠር የግጭት መንስኤ የሰው ልጅ ህይወት መጥፋት አላስፈላጊ ነው፤ ኢትዮጵያ ግጭትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ  ባህልና ወግ ያላት ሲሆን አንዱ አንዱን ደግፎ የሚታይበት እንደ መሆኑ ያለመግባባቶችን ወደ ጎን በመተው የሀሳብ ልዩነቶችን ወደ መድረክ በማምጣት ባህላዊዉንና ሳይንሳዊ መንገዶችን በመጠቀም መከለከልና ማስተዳደር ይገባል በማለት ሰነዱን መነሻ በማድረግ አብራርተዋል።