የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል
የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል የ2017 ዓ/ም 1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ
ጥቅምት 28/2017 ዓ/ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል የ2017 ዓ/ም 1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።
የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በቢሮው በጀት፣ዕቅድ ዝግጅት፣
ክትትልና ግምገማ ደይሬክተር በአቶ ማስረሻ ሃብቴ ቀርቧል።
በሪፖርቱ የሩብ ዓመቱ ውስጥ ባሕላዊ ፣ኃይማኖታዊ ና ሕዝባዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ መደረጉ፣በከተማው ውስጥ የፀጥታ ስጋት የነበረው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሠጣጥ መፍትሔ ማግኘቱ፣ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሠሩ ቅንጅታዊ አሠራሮች በጥንካሬ የተነሱ ሲሆን የቢሮው የዕቅድ አፈፃፀም የተሻለ መሆኑ ተጠቅሷል።
በቢሮው ከማዕከል እስከ ወረዳ እያጋጠሙ ያሉ የሰው ኃይል ዕጥረትና የቢሮ ጥበት ችግሮች አሁንም ባለፈው ሩብ ዓመት ችግር ሆነው የዘለቁ ስለሆነ በቀጣይ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ በሪፖርቱ ቀርቧል።
የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚሁ መድረክ ላይ ባስቀመጡት የትኩረት አቅጣጫ ባለፈው ሩብ ዓመት ያጋጠሙት የሰው ኃይልና የግብዓት ዕጥረቶችን በመቅረፍ የላቀ አፈፃፀም ማስመዝገብ፣አገልግሎት አሰጣጣችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማሳደገፍ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ የአሠራር ሥርዓት የአፈፃፀም ደረጃን ማሻሻል፣ የፀጥታ ኃይሎችን የወንጀል መከላከል አቅምና የአፈፃፀም ደረጃ የላቀ እንዲሆን አብሮ መሥራት፣በዘላቂ ሰላም ግንባታ ለይ ሕብረተሰቡ ግንዘቤ ማሳደግ ማሳተፍና ንቅናቄ መፍጠር፣ ወዘተ በቀጣይ አጠናክረን መሥራት ይገባናል ብለዋል።