"ግጭትን ማስተዳደርና ሰላምን መገንባት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
የከተማችን ዕድገት ብሎም የእትዮጵያ ከፍታ የሚመጣው በአብሮነት ውስጥ ስለሆነ ሁላችንም መለያየትና ቂም በቀል ትተን በአንድነት እንቁም
አቶ ሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታአስተደደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ
ጥቅምት 30/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
"ግጭትን ማስተዳደርና ሰላምን መገንባት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለተለያዩ አደረጃጀቶች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡
በዛሬው ውሎ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የትምህርት ቤት የሰላም ክበባት ሰብሳቢ ተማሪዎችና ተጠሪ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ እንደተናገሩት ትምህርት ቤት ትውልድ የሚገነባበት ሥፍራ ስለሆነ ትልቅ ትኩረት ስለሚያስፈልግ አከባቢው ያለምንም አዋኪ ድርጊቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታ ሊኖረው ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይ ቁማር ቤቶች ሺሻ፤ጫት ቤቶች፤ መጠጥ ቤቶች ከትምህርት ቤቶች ሊርቁ ይገባል ካሉ በኃላ ቤቲንግ ቤትን በተመለከተ በለፈው በጀት ዓመት ሰፊ ስራ መሰራቱ ይታወቃል፤ አሁንም ለመማርና ማስተማር ሥራ እንቅፋት የሚሆኑ አወኪ ድርጊቶችና ሌሎች ጉደዮች ላይም እየተሰራ ነው ካሉ በኃላ የከተማችን ዕድገት ብሎም የእትዮጵያ ከፍታ የሚመጣው በአብሮነት ውስጥ ስለሆነ ሁላችንም መለያየትና ቂም በቀል ትተን በአንድነት እንቁም ብለዋል።
መድረኩ ላይ በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ ቡድን መሪ አቶ ልቅነው ታሪኩ፦ አዋንታዊ እና አሉታዊ ሰላም፣ የግጭትና የሁከት ፅንሰ ሃሳብ፣ መዋቀራዊ ሁከት መገለጫ፣ የግጭት ዕድገት ሂደት፣ የግጭት አይነቶች፣ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች፣ ከሰላም ክበባት ምን እንደሚጠበቅ ...ወዘተ በዝርዝር አብራርተዋል።