የ2017 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ2017 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ከተጠሪ ተቋሙ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር

በከተማው ላይ ህብረተሰቡ ያሳተፈ ስራ በመሰረቱ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል ።

 ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ

ህዳር 2/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

******

ሀላፊዋ ይህንን የተናገሩት ቢሮው የ2017 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ከተጠሪ ተቋሙ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በገመገሙበት መድረክ ላይ ነው ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማው ላይ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴዎች እየተሰሩ በመሆኑ የለማችና ሰላም የሰፈነባት ከተማ ከማድረግ አንጻር ለውጥ እየታየባት ይገኛል ብለዋል።

ከተማዋ የአፍሪካ ተምሳሌት እና ተመራጭ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ እንድትሆን ከማድረግ አንጻር ህብረተሰቡን በማሳተፍ፤ ከጸጥታው አጋዥ ኃይሎች ጋር በመሆን የሰላም ዘብ እንዲሆኑ በመደረጉ ያለፉት ትላልቅ የአደባባይ በዓላቶች ወንድማማችነትንና አንድነትን ባጸና መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ከማድረጉም በላይ በከተማው ላይ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።

ለጸጥታው መደፍረስ ስጋት የነበሩ ወንጀሎችንና የደንብ መተላለፎችን፣ደንብና ህጎችን በማውጣት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ በጸጥታው ስራ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ጠቁመዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም የጸጥታ ስራ ተለዋዋጭነት ስላለው ባለመዘናጋት የሰላም፤ የጸጥታና የደህንነት ስራው ተጠናክሮ ህገ-ወጥ ተግባራትን የሚፈጽሙና ለከተማው ሰላም መደፍረስ ምክንያት የሆኑ አካላት ላይ ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ከግዜ ወደ ግዜ ለውጥ ያለው ስራ እንደ ተቋምም እንደ ከተማም እየተሰራ እንደመሆኑ መጠን የጽንፈኛ ሀይሎችን አመለካከቶች የማክሸፍ ስራ በመሰራቱ የተሻለ ውጤት ማምጣት መቻሉን ገልፀው በአዋኪ ድርጊት ዙሪያ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደ ሁሉ የወንጀል ድርጊቶች ላይም በትኩረት በመስራት አሁን ያለውን የወንጀል ከስተት ምጣኔን መቀነስና የተጀመሩ ልማቶችን ማፋጠን ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።