ለባለ ባጃጅ እና ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ ማ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለባለ ባጃጅ እና ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ ማህበራት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ ።

የቢሮው የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ለባለ ባጃጅ እና ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ ማህበራት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ ።

ጥር 5/2016ዓ.ም (አዲስ አበባ )

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የባጃጅና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ማህበራት ስልጠና ተሰጥቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከባጃጅና ሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ማህበራት ጋር ምክክር አድርጓል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የከተማዋን የትራንስፖርት አጥረት በመቅረፍ እና ረጃጅም የታክሲ ሰልፎችን በማስቀረት አማራጭ መሆናቸውን አንስተዋል።

ነገር ግን ወጥ የሆነ የቁጥጥር አሰራር ባለመዘርጋቱ አንዳንድ የባለ ሶስት እግርና የሞተር ተሽከርካሪ ባለንብረቶች በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የፀጥታ ስጋት ሆነው ቆይተዋል ብለዋል።

ቢሮው በህጋዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ከ1970 የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን እንደ አዲስ ማደራጀት ተችሏል ብለዋል።

እነዚህ አካላት ህግና ስርዓትን ከማክበር በተጨማሪ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ወንጀልን የመከላከል ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

የሰላም ዋጋ ቅድሚያ የሚሰጠው እንደመሆኑ መጠን ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ህግና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገቢነት ስላለው አንዱ ስለ ሰላም ሲሰራ ሌላው ሰላምን ማደፍረስ እንደሚሰራ የሚታወቅ ሲሆን ህግና ስርዓት ጠብቆ በመንቀሳቀስ የሰላሙ አገልጋይ መሆን ይገባናል ሲሉ የቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ጠቅሰው ወንጀሎች ሲፈጸሙ ዝም ከማለት ይልቅ ወንጀለኛን በማጋለጥ ህግና ስርዓትን ከማክበር በተጨማሪ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ወንጀልን መከላከል የሁለም ኃላፊነት መሆን ይገባል በማለት ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የመጡት

አቶ አሸናፊ ስዩም በበኩላቸው በቀጣይ በይበልጥ ተቀናጅቶ በመስራት ህግን የማስከበር ተልዕኮን መወጣትግዴታችን እንደመሆኑ መጠንና ጸጥታን መጠበቅ የዜግነት ሀላፊነትን መወጣት በመሆኑ ከ አጋዥ አካላት ጋር አሁንም መመሪያን በጠበቀ መልኩ መስራት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።