የ1ኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አሠራር የዕቅድ አፈፃፀም ከ29 የባለድርሻ አካላት ጋር
በከተማችን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በባለድርሻ አካላትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በተሰራ ሥራ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የህዳር 05/2017ዓ.ም
(አዲስ አበባ)
የቢሮ ሀላፊዋ ይህንን የተናገሩት ቢሮው የ2017 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አሠራር የዕቅድ አፈፃፀም ከ29 የባለድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት መድረክ ላይ ነው ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በሰላም ማስከበር ላይ ቅንጅታዊ አሰራሮች በመዘርጋትና በመገምገም በከተማችን ላይ ዘላቂ የሰላም እንዲመጣ በትኩረት በመሥራታችን ውጤት ሊመዘገብ ችሏል ብለዋል።
በከተማችን የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ንግድ፣ጤናማ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዳይኖር የሚያደርጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ክግድ ቢሮ ጋር፣በት/ቤቶች ዙሪያ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከሚያስተጓጉሉ አዋኪ ድርጊቶች ከት/ት ቢሮ ጋር፤ በመሆን በርካታ ሥራዎች በቅንጅት ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡
በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የትራንስፖርት እጥረትና የዋጋ ጭማሪ፣በተለይም ከባጃጅ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን፣ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚፈፀሙ የመሬት ወረራዎችን ከአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመነጋገር ሕግና ስርዓት እንዲያስያዙ መሰራትንና ሌሎች ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮችም መቀነስ መቻላቸውንም ገልፀዋል።
የ2017 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አሠራር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት የቢሮው ም/ል ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ ሲሆኑ፣በገለጻቸውም በሰላምና ፀጥታው ጉዳዮች ዙሪያ ህዝቡን ተሳትፎ ማሳደግ፣ለፀጥታ ስጋት የሆኑ በታዎች ከስጋት ነጻ ማድረግ፣ፖሊሲዎች መመሪያዎች እና ደንቦችን አዘጋጅቶ እንዲፀድቁ ማድረግ፣የኢኮኖሚ አሻጥርን ለማስቀረት በልዩ ትኩረት መሰራቱን አብራርተዋል።
በቀጣይም ከት/ት ቤቶች ጋር ተያይዞ አዋኪ ድርጊቶችን ተከታትሎ በማስወገድ፤ የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር የሰላም ክበባትን በማጠናከር ተማሪዎች የሰላም ምንነት፣ህብረ-ብሔራዊ አንድነትንና አብሮነትን እንዲያውቁ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።