የፎቶ አውደ ርዕይ
የቢሮው ሰራተኞች የብልጽግና ፖርቲ አምስተኛ አመትን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ ጎበኙ።
ህዳር 13/2016ዓ.ም (አዲስ አበባ )
*******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ "የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ የተዘጋጀውን የብልጽግና ፖርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የከተማው የኮሪደር ልማት ስራዎች፣የተማሪዎችና የተስፋ የምገባ ማዕከላት፤ ሆስፒታሎች፣የትምህርት ቤቶችና የመኖሪያ ቤቶች የመገንባትና የማስፋፋት፣ሰፋፊ የሆኑ የመንገድ፤ የውሀ ፕሮደክቶች፤ የነገዋ የሴቶች ማበልጸጊያ ማዕከላት ፕሮጀክቶች ዓለማቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች፤ የእንስሳትና ልማት ማዕከላት፤
ቅሻሻዎችን በዘመናዊ መልኩ የማስወገድና መልሶ መጠቀም የሚያስችሉ ወዘተ...ተግባራት የተከናወኑበትና እየተከናወኑም የሚገኙ እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ለዕይታ ከቀረቡ ፎቶዎች ለማወቅ ተችሏል።
በአውደ ርዕዩም ከፎቶ በተጨማሪ፤የሰርቶ ማሳያ ሞዴሎችና የቨርቹዋል ማሳያዎችን በመጠቀም ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ በፓርቲው አመራር አዲስ አበባ ስሟን በሚመጥን የዕድገትና የለውጥ ጎዳና ላይ፤የቱሪዝም ማዕከል፤ለኑሮ ምቹ፤ ዓለማቀፍ ደረጃዎችን ያሟላች ከተማ ለማድረግ በሰፊው የተሰራና አሁንም እየተሰራ እንደሆነ ለማየት ተችሏል።