በወንጀል መከላከል ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና

image description
- recent news   

በወንጀል መከላከል ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና

ከኮንዶሚኒየም ማህበራት ሰብሳቢዎች ጋር በወንጀል መከላከል ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ተካሄደ።
                             
   ህዳር 14/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
                ******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ውስጥ ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ  ቤቶች ማህበራት
ሰብሳቢዎች  ጋር ግምገማዊ ስልጠና አድርጓል።

በግምገማዊ ስልጠናው ላይ ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው የፀጥታ የኦፕሬሽን ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው ሲሆኑ፤የግምገማዊ ስልጠናው ዋና ዓላማ  ተወካዮቹ ስለ ወንጀል ምንነት፤ስለወንጀል መከላከልና አሁናዊ የከተማው የፀጥታ ሁኔታ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሯቸው ለማህበራቱ አባላት በተዋረድ መረጃውን እንዲያጋሩና ፣በጋራ መኖሪያ ቤት አከባቢ የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን መለየት የነዋሪውን ደህንነትና ሰላም እንዲጠበቅ ለማስቻል ነው ብለዋል።
 
በሰነዱም የወንጀል መከላከል አስፈላጊነት፣ወንጀል በግል ህይወትና በአገር ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት፤
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራትተወካዮች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባው ቅንጅታዊ አሰራር ወዘተ..ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ አብዲሳ አራርሶ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ እየተፈጸሙ ያሉት የፀጥታ ችግሮች ከሁሉም ሳይቶች ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ጠቅሰው፣በአከባቢው ላይ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጥናት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለውም ከአከራይ ተከራይ ጋር ተያይዞ በህገ-ወጥ መንገድ የሚሠሩ አንዳንድ ሳይቶች መታረም ይገባዋል፤ከወረዳ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ችግሮችን መፍታት እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥተው አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስደዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ፣የሚቀጠሩ የጥበቃ ሠረተኞች በጥንቃቄ ሊመለመሉ ይገባል ፣ፀጉረ ለውጦችን በንቃት ማየትና መፈተሽ፤አከራዮች ትኩረት ሰጥተው የሚከራየውን ሰው ማንነት በመለየት ህግና ደንቡን በጠበቀ መልኩ እንዲከራዩ ማድረግ ያስፈልጋል ካሉ በኃላ በጋራ መኖሪያ ቤቶች  ዉስጥ የሚስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶችን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ  በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥናትን መሰረት ያደረገ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ም/ል ቢሮ ኃለፊው ተናግረዋል፡፡

አብራችሁን ሰለቆያችሁ እናመሰግናለን!