19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን

ቢሮው 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበረ።

ህዳር 16/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አመራርና ሠራተኞች "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከብረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔርና ብሔረሰቦች ሀገር እንደመሆኗ መጠን አሁን ያለው ሥርዓት ሁሉንም ብሔር በዕኩል የሚያይና የሚያስተዳድር ነውም ብለዋል፡፡ በተለይም አዲስ አበባ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ

ባት ከተማ ስትሆን የህብረ ብሄራዊ አንድነትን መርህ በተከተለ መንገድ መብታቸው ተጠብቆላቸው በመቻቻል የሚኖሩባት ከተማ ስለሆነች ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይም በዓሉን በማስመልከት አቶ ኤሊያስ ቀጄላ የቢሮው የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ አሰልጣኝ ህብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ፤ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ ሃሳቦች፤ ፌደራል የፖለቲካ ሥርዓት፣ የህብረ ብሔራዊ ስርዓታችን ግንባታ፣ወዘተ... በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰነድ አቅርበው ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።