ስለ አገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድ ምዘገባና ንጽጽር ስልጠና
ዕቅድን በየደረጃው ስለማውረድ፤ ስለ አገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድ ምዘገባና ንጽጽር ስልጠና ተሰጠ ።
ህዳር 17/2017ዓ.ም (አዲስ አበባ )
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የተቋማት ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች እና ለሁሉም ክ/ከተማ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች በካስኬድ እስታንዳርድ ምዘገባና ንጽጽር ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
አቶ ገብሬ ዳኝው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አማካሪ በመግቢያው ላይ እንዳሉት ሥራን በዘመቻ መስራት አመርቂ ውጤት እንደማያመጣ ጠቅሰው የተቋም ሰራተኞች በዕቅድ በመመራትና በቴክኒክ ስራዎች ላይ በቂ ዕውቀት በመያዝ በአፈፃፀማቸው ብቁና ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
የቢሮው አማካሪ አክለውም ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ መሰረተ-ልማቶችን ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ በጉዳዩ ላይ ሥልጠናዎችን እስከታችኛው መዋቅር በመስጠት ወደ ተሟላ ትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ቢሮ የአግልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ የታቀደን ዕቅድ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማረድ፤በመለካትና የአፈፃፀም ደረጃን ወደላቀ ማሳደግ፤ የሚታዩ ክፍተቶችን ለይቶም በማወቅ ውጤት ተኮር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ በመጠቆም ቅልጥፍናንና ውጤታማነትን አሟልቶ በመስራት የተቋሙን ቁልፍ ዓላማና ግብ ማሳካት አስፈላጊ መሆኑን በገለፃቸው ጠቁመዋል።