በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ።
ህዳር 17/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ተቋሞች ጉዳዮች ዘርፍ በሃይማኖት ተቋማት የሚስተውሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርሰቲያን የአዲስ አበባ ሃጉረ ስብከት ጋር ውይይት አድርጎል።
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃጉረ ስብከትን በሚመለከት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፈፍታት እንዴት እና ማን በሃላፊነት እንደሚፈታ ተወያይተዋል።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት የውስጥ ችግሮችን በራሳቸው በመፍታት እና መጪው የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ የጥምቀት በዓል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሃይማኖታዊ ትውፊቱ ጠብቆ በሚከበርበት ሁኔታ ላይ በመመካከር ከበዓሉ ማክበሪያ ሥፍራዎች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ከወዲሁ ለይቶ መፈታት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት ቢደረግም በሌሎች የኃይኖት ተቋማት አከባቢ የሚስተዋሉ ተመሳሳይ ችግሮችን በቀጣይ በየደረጃው ውይይት የሚደረግባቸውና ችግሮችና በመናበብ በጋራ የመፍታት ጥረቱ እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፤ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፃሃፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መ/ር የማነብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ኤሴት ግንባታ ዘርፍ ዳሬክተር አቶ ተመስገን እጅጉና የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የክፍለ ከተሞች መምሪያ ሃላፊ አቶ ለሜሳ ጉተታ ተገኝተዋል።