የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና

ሰላም የሚገነባው አየር ላይ በመነጋገር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ሚመነጭ የሰላም ወዳድነት ስሜት ጭምር ነው።

* የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ

ህዳር 18/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የጫኝና አውራጅ ማህበራት አባላት "ግጭትን ማስተዳደርና ሰላምን መገንባት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ የሰላም ዋጋ በምንም የማይተመን የሁሉም ነገር መሰረት ስለሆነ የሚገነባውም አየር ላይ በመነጋገር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ በሚመነጭ የሰላም ወዳድነት ስሜት መሆን አለበት ብለዋል።

ከዚህ ስልጠና በኃላ የሚጠበቀው ውጤት ግጭትን የመፍታት አቅም መጨመር፣ በመደጋገፍና መደማመጥ አብሮነትን መጎልበት ነው ብለዋል።

መድረኩ ላይ በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ ቡድን መሪ አቶ አብርሃም እንግዳወርቅ አውንታዊ እና አሉታዊ ሰላም፣ የግጭትና የሁከት ፅንሰ ሃሳብ፣ የግጭት ዕድገት ሂደት፣ የግጭት መንስዔዎች፣ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች... ወዘተ ላይ በዝርዝር አብራርተዋል።

አቶ አብረሃም በማብራሪያቸውም አንዱ የግጭት መንስዔ አለመተማመን ነውና ስራችንን በመተማመን እና በመተሳሰብ መስራት ይኖርብናል። ሁከት ለልማትና ለእንድገት መሰናክልና የሃገር ገፅታን የሚያበላሽ ስለሆነ ሁላችንም በየአካባቢያችን ግጭትን በሰላማዊ መንንገድ መፍታት ይኖርብናል ብለዋል።

መድረኩን የመሩት የቢሮው የሕዝብ አደረ ጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሮፍሬሕይዎት በለጠ እንደተናገሩት ግጭት ሳይከሰት በፊት አመላካች ሁኔታዎችን በማየት አስቀድሞ መከላከል፣ከተከሰተም ባህላዊና ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በስራ ቦታ ላይ ሁሉም ጫኝና አውራጅ የመለያ ልብስ መልበስ፣ ከዋጋ ተመን በላይ የሚሰሩ ካሉ ለይቶ መጋለጥ፣ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እና የውስጥ ችግሮችን አብሮ ተወያይቶ መፍታት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።