በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የታክሲ ተራ አስከባሪ እና ለፓርኪንግ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ውይይት ተካሄደ ።
በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የታክሲ ተራ አስከባሪ እና ለፓርኪንግ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ውይይት ተካሄደ ።
ህዳር 19/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የታክሲ ተራ አስከባሪ እና የፓርኪንግ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ተወካዮች "ግጭ ትን ማስተዳደርና ሰላምን መገንባት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ዉይይት ተካሂዷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን ያቀረቡት የዘርፉ ባለሙያ አቶ ውድነህ አቢ ሲሆኑ አዎንታዊ እና አሉታዊ ሰላም፣ የግጭትና የሁከት ፅንሰ ሃሳብ፣ የግጭት ዕድገት ሂደት፣ የግጭት መንስዔዎች፣ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ላይ በዝርዝር አብራርተዋል።
አቶ ውድነህ አያይዘውም እንደገለጹት አንዱ የግጭት መንስዔ ከሆኑ ነገሮች መካከል አለመተማመን፣መራራቅ፣ መለያየት፣ግላዊ ባህሪ ወዘተ... ሲሆኑ መንስዔዎቹን ለይቶ በማወቅ ስራዎችን በመተማመን በመተሳሰብና በመረዳዳት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የግጭት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ተባብሶ ወደሁከት፣ብጥብጥና ጦርነት ሳይቀየር መንስኤዎችን በቅድሚያ ለይቶ በባህላ ዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በመጠቀም በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።
ዉይይቱን የመሩት የቢሮዉ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ልቅናዉ ታሪኩ እንደተናገሩት ከቀረበዉ ሰነድና
ከተሳታፊዎች ከተሰነዘረዉ ሃሳብ በመነ
ሳት በታክሲ ተራ ማስከበር ቦታዎች ላይ ታክሲዎች አቆራርጠው ሲጭኑ፣ዋጋሲጨ
ምሩና ሕብረተሰቡን ሲያንገላቱ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባ
በር እንደመፍታት ችግሩን የሚያባብሱና ሕብረተሰቡን የሚያማርሩ የተራ አስከባ
ሪዎች ስላሉ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆ ጠቡ አሳስበዋል።