ለቢሮው እውቅና ተሰጠው።

image description
image description
image description
- recent news   

ለቢሮው እውቅና ተሰጠው።

ቢሮው በዲስ አበባ ከተማ ተካሂዶ የነበረው የዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የሃይማኖትና የሰላም ኮንፈረንስ በሰላም በመጠናቀቁ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው።

ህዳር 20/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዶ የነበረው የዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የሃይማኖቶች ጉባኤ በሰላም በመጠናቀቁ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሰላም ሚኒስቴር እውቅና ተሰጥቶታል።

ለቢሮው ዕውቅናው የተሰጠው ለኮንፈ

ረንሱ መሳካት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ ግብር ባዘጋጀበት መድረክ ላይ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ጫኔ የቢሮው ም/ል ኃላፊ ገልፀዋል።

የተካሄደው የአለማቀፍ እና አገር አቀፍ የሃይማኖትና የሰላም ኮንፈረስ ለከተማው ገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅዖ በማድረጉና አጠቃላይ ፕሮግራሙ በሰላም ተጀምሮ በሰላም በመጠናቀቁ ላበረከተው አስተዋፅዖ የተሰጠው እውቅና መሆኑን አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ዕውቅናው የተሰጠው ለኮንፈረንሱ መሳካት ከላይ እስከታች የሚገኙ የቢሮውከፍተኛአመራሮች፣ደይሬ

ክተሮች አስተባባሪ ዎች፣ቡድን መሪዎች፣

ፈፃሚዎች፣ ባለድርሻ አካላትና መላው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ስለሆነ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁብለዋል።