ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተው ጣጡ የዕድር ምክር ቤት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናተሰጠ።
ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶች እና የመፍ
ትሄ ሐሳቦች ፅንሰ ሃሳብ ላይ በአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተው
ጣጡ የዕድር ምክር ቤት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናተሰጠ።
ህዳር20/2017ዓ.ም(አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴትግንባታና የሃይ ማኖት ተቋማት ጉዳዮች ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የዕድር
ምክር ቤት አመራሮች ስልጠና ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታአስተዳደር ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበትወቅት የስልጠናዉ መሰረታዊ ዓላማ ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሐሳቦች በሚል ፅንሰ ሃሳብ ላይ ሲሆን፣ይህም ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች መካከል አንዷ ስለሆ
ነች ዜጎች በጉዳዩ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ማድረግ በማሰ ፈለጉ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ተናግ ረዋል።
የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖትጉዳዮች
ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ የፌደራል ስርዓቱን ለመገን
ባትመሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር፣በፌደራል ስርዓቱ የዴሞ ክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ለመብቶች መከበር፣ህብረ-ብሔራዊ ስርዓታችንን ግንባታ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶ
ችና መፍት ሔዎቻቸው ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ውይይቱን የመሩት የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ተመሰገን እጅጉ እንደተናገ
ሩት ፌደራሊ ዝም ስንል በጋራ ተከባብረንና ተቻችለን ለመኖር የገባነው ቃል ኪዳን እንደሆነና፣ የህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከ ሪያ ሀረግ ነው ብለዋል።
አቶ ተመስገን አክለውም የዕድር ምክር ቤት አባላት ለሀገር ግንባታና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ስለሆነ ያገኙትን ግንዛቤ ለአባሎቻቸው በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።