"ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች" በሚል ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

"ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች" በሚል ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ህዳር 25/2017ዓ.ም (አዲስ አበባ )

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴትግንባታና የሃይማኖት ተቋማት ጉዳዮች ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ ወጣት ማህበር ተወካዮች "ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣

ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች" በሚል ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጠቷል ።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደተናገሩት እንደ ሀገር የፌደራሊዝም ስርዓትን በመጠቀማችን ያገኘነው ጥቅም እጅግ በጣም በርካታ ከመሆኑም ባሻገር ስርዓቱ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት ማለት ይቻላል ካሉ በኃላ ሀገራችን ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የሚገኙባትና የሚኖሩባት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ የሚታዩ አለመግባባቶች ቢኖሩም መከፋፈሉን ትተን ወደ አንድነት መምጣት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ወጣቶች የነገው ሀገር ተረካቢ እንደመሆናችሁ መጠን የዛሬዋና የነገዋ ኢትዮጵያ አንድነትን አጽኚ ኃይል በመሆናችሁ ተስፋ የሚጣልባችሁ ናችሁ፤በአብሮነት፤መረዳዳትና በመተጋገዝ ውስጥ የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም በመቀራረብ በመወያየትና በመቻቻል ልዩነቶችን በማጥበብ ዘላቂ ሰላምን ማፅናት ይጠበቅባችኃል ብለዋል፡፡

የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳ

ዮች ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ እንዳሉትም የፌደራል ስርዓቱን ለመገንባትና መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን መፍጠር፣በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ለህግ የበላይነት መረጋገጥ፤ለመብቶች መከበር፣ለህብረ-ብሔራዊ ስርዓታችንን ግንባታ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ውይይቱን የመሩት የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ተመሰገን እጅጉ እንደተ

ናገሩት ፌደራሊዝም በጋራ ተከባብረንና ተቻችለን ለመኖር የገባነውን ቃል ኪዳን እንደሆነና ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለዲሞክራሲን ሥርዓት ግንባታ የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማበርከት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፣ከሁሉም ክ/ከተማ የተወጣጡ ወጣት ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል ።

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የዕድር ምክር ቤት ሃላፊዎች ስልጠና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡