የቀጠለ ስልጠና

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቀጠለ ስልጠና

ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች በሚል ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ ሲሰጥየነበረው ስልጠና ዛሬም ቀጥሏል ።

ህዳር 26/2017ዓ.ም(አዲስ አበባ )

***

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት

ጉዳዮች ዘርፍ ከሁሉም ክፍለ ከተማ

ለተውጣጡ ሴት አደረጃጀቶች ተወካዮች ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት

በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች በሚል ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል ።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደተናገሩት እንደ

ሀገር በብዙ ነገር ብንለያይም አንድ ሊያደ

ርጉን የሚችሉ ነገሮች ደግሞ በጣምብዙ በመሆናቸው ሚዛን ጠብቆ በፍትሃዊነት ለማስተዳደር የፌደራል ሥርዓት አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል ስርዓቱ ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥ

ንትነው ስንል እራስን በራስ የማስተዳደር መብትም ከህገ-መንግስታችንና ከፌደ

ራል ሥርዓታችን የመነጨ ስለሆነ ነው ካሉ በኋላ ሴቶች ደግሞ ቤተሰብንና ሀገርን የመምራት አቅም ስላላቸው በየዘርፉ የአመራር ሚናቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል፡፡

የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖትጉዳዮች ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ እንዳሉትም የፌደራል ስርዓቱን መገን

ባትና መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ መግባባት፣የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣የህግ የበላይነት መረጋገጥ፤

ለሰው ልጆች መብት መከበር፣የህብረ-

ብሔራዊ ስርዓታችን ግንባታ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው በሚሉ ርዕሶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን እጅጉ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ፌደራሊ

ዝም ተከባብረንና ተቻችለን የምንኖባት

ስርዓት እንደመሆኑ መጠን ልዩነታችንን ትተን የሀገራችንን አንድነት ማስቀ

ጠል ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል።

የተለያዩ የጽንፈኝነትን አስተሳሰብን ትተን በኔነት ስሜት የአገራችንን መጻኢ ዕድል የተሻለ ለማድረግ ሴቶች ሚናችሁ ከፍ

ተኛ ስለሆነ በርትታችሁ ለሰላም መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ተናግረዋል።