በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አከባቢ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቶች እንደይቀጥሉ የሚያውኩ የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ ተወሰደ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አከባቢ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቶች እንደይቀጥሉ የሚያውኩ የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ ተወሰደ፡፡
ህዳር 26/2017ዓ.ም(አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የጫት ቤቶችና ፔንሲዮን ቤቶችን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ 879 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል።
በዚህም አዋኪ ድርጊት በፈፀሙ በ184 ጫትና ሺሻ ቤቶች፣ 112 ግሮሰሪ፤ በ106 አረቄና ጠጅ ቤቶች፣ በ48 ግሮሰሪ መጠጥ ቤቶች፣ 12 ፔንሲዮን ቤቶች፣ 120 ፑል ማጫወቻ ቤቶች፣ በ122 የድምፅ ብክለት ያለባቸው ሙዚቃ ቤቶችና ቪዲዮ ቤቶች እንዲሁም በ171 ሌሎች የንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን በዝርዝር አስረድተዋል።
እርምጃ የተወሰደው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ ለማድረግ እንደሆነም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል ።
እርምጃው የተወሰደው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከትምህርት ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ፣ ፓሊስና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር የጋራ ግብረ ሃይል በማቋቋም በተደረገው ጥናት የተሰራ ኦፕሬሽን እንደሆነም ተገልጿል።