የቢሮው የማሻሻያ ጥናት ተገመገመ

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሮው የማሻሻያ ጥናት ተገመገመ

የቢሮውን የአገልግሎት አሰጣጥ አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እየተዘጋጀ ያለው የማሻሻያ ጥናት ተገመገመ

ሕዳር 28/2017 ዓ/ም (አዲስ አበባ)

*******

የቢሮውን የአገልግሎት አሰጣጥ አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በአዳማ ከተማ እየተዘጋጀ ያለው የማሻሻያ ጥናት በስትራቴጂክ ማኔጅመንት አባላት ተገምግሟል።

ቢሮውን በአሠራር፣በአደረጃጀትና በሰው ኃይል በማሻሻል እስካሁን በነበረው አሠራር ወቅት ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ሊፈታና የአገልግሎት አሰጣጡን ሊያሳልጥ የሚችል አሠራርን ለማሻሻል ከተለያዪ የሥራ ክፍሎች አጥኚ ቡድን በማቋቋም ጥናቱ ሲሰራ እንደነበር ታዉቋል።

አጥኚ ቡድኑ የቢሮው የመዋቅር ማሻሻያ ፣የመሠረታዊ ሥራ ሒደት ክለሳ፣ የአደረጃጀት መዋቅርና፣የሕግ ማዕቀፍን ያካተተ ጥናት ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል።

አጥኚ ቡድኑ እስካሁን የሠራቸውን የጥናት ሥራዎች ሪፖርት አቅርቦ በስትራቴጂክ ማኔጅመንቱ ተገምግሟል።

ስትራቴጂክ ማኔጅመንቱም ከቀረበው የጥናት ሪፖርትና የተቋሙ አሁናዊ የመፈፀም ብቃትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ግብዓቶችን አጥኚ ቡድኑ በሚሠራው ጥናት ውስጥ እንዲያካተት አንዳንድ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።