ቢሮው በሲቪክ ማህበራት አደረጃጀት እና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ቢሮው በሲቪክ ማህበራት አደረጃጀት እና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ህዳር 30/2017ዓ.ም
*****
(አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህብረተሰብ ተሳትፎና የቡዝኃን ማህበራት ዘርፍ በቢሮው ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በሲቪክ ማህበራት አደረጃጀትና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናውም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታአስተዳደር ቢሮ ም/ል ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የዛሬው ስልጠና ቢሮው የሲቪክ ማህበራትን ለመደገፍ የጠራ መረጃ መያዝና ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው አደረጃጀቱ ከቢሯችን ጋር በቅርበት በሚሠሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል።
የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የኢፌድሪ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን ሲሆኑ በገለጻቸውም፣የሲቪክ ማህበራት ምንነትን፣አደረጃጀትና አሠራር ሁኔታ አብራርተዋል።
እነዚህ በሲቪክ ማህበራት የተደራጁ ቡዙኃን ማህበራት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከሰላምና ፀጥታ አኳያ እንዴት ከቢሮው ጋር መስራት እንዳለባቸውና ቢሮውም በምን መልኩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዳለበት አቶ አሉላ በሰነዳቸው አብራርተዋል።