በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች የሰላም ኮንፈረንስ ሲካሄድ ዋለ፡፡
በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች የሰላም ኮንፈረንስ ሲካሄድ ዋለ፡፡
ታህሳስ 01/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
"ሀገር ወዳድነትና የሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የግንባር ቀደም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ የተዘጋጀው ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለተ በሁሉም ወረዳዎች ሲካሄድ መዋሉ ታውቋል፡፡
በሁሉም መድረኮች ላይ ስለ ሀገር ወዳድነት ስለ ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ህብረተሰቡ ከተማውን ብሎም የሀገሩን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንደካሁን በፊቱ ሁሉ ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋገጠበት መድረክ ሆኖ መዋሉ የታወቀ ሲሆን ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች ደረጃ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አመልክቷል፡፡