የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረታዊ ነገሮችና ብሔራዊ እሴቶቻችን " በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች "ሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረታዊ ነገሮችና ብሔራዊ እሴቶቻችን" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት የዘርፉ አሰልጣኝ አቶ ኤልያስ ቀጄላ ሲሆኑ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ብሄራዊ ዕሴቶቻችንና ጥቅሞች፣
አንዲሁም የሌሎች አገራት ተሞክሮ፣....ወዘተ በዝርዝር አብራርተዋል፣ አሰልጣኙ አቶ ኤልያስ በማብራሪያቸው ያለ ሰላም ልማት ስለሌለ ዋናው ብሄራዊ ጥቅማችን ማስከበሪያ መነገድ አንዱ ሰላምና ደህንነታችንን ማረጋገጥ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል።
መድረኩን የመሩት ም/የቢሮ ሃላፊው አቶ ተስፋዬ ጫኔ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሌላውን ፍላጎትና ማንነት ረግጦ የአንዱን ጎላ የአንዱን ለማኮሰስ ሳይሆን የሁሉም ማንነት፣ ብሔር እና ሃይማኖት በእኩልነት ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን ይገባል ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለውም የሀገረ መንግስት ግንባታ ሥራችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ማለትም በኤኮኖሚ፤በፖለቲካ፤በማህበራዊ፤በዲፕሎማሲ፤
በትምህርትወዘተ... መሆን እንደሚገባ ጠቁመው፤አገርን ከማገልገል በላይ የሚያኩራ ነገር ስለለሌ ሁላችንም በተመደብንበት የሥራ ዘርፍ በፍቅር ማገልገል አለብን ብለዋል።