ለነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች ስልጠና...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች ስልጠና ማስጀመሪያ በድረክ

በከተማው ላይ አሁን ላለው ሰላምና ጸጥታ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው የሰላም ሰራዊቱ ነው።

•ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳ

ደር ቢሮ ሀላፊ

ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ )

********

ክብርት የቢሮ ሀላፊዋ ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች ስልጠና ማስጀመሪያ በድረክ ላይ ነው።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ቢሮው የተለያዩ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ከተፈጠሩት አደረጃጀቶች መካከል በከተማው ላይ አሁን ላለው ሰላምና ፀጥታ ኩራት የሆነውና የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው የሰላም ሰራዊቱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አልፎ አልፎ በተለያዩ አከባቢዎች የሚስተዋሉ የጸረ ሰላም ሀይሎች ሁከትና ብጥብጥ በአዲስ አበባ ያልተከሰተው ይህ አደረጃጀት ከፀጥታ ኃሎች ጋር በመቀናጀት አከባቢውን በንቃት በመጠበቁ ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በከተማ ውስጥ ዓይነታቸውን በመቀያየር አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ወንጀሎችን ከወትሮ በተሻለ ዘግጁነት ነቅተን በመጠበቅ የከተማችንን ነዋሪ ከወንጀል ስጋት ነፃ ልናደርግ ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

ምክትል የቢሮው ኃላፊው አቶ ሚደቅሳ ከበደ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታው መዋቅር ጋር በመሆን ከተማዋ ሰላሟ የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል።

የማነቀቂያ ስልጠናው በሰባት መርሃ-ግብሮች የሚከናወነው ሲሆን በሰላም ሰራዊት አደረጃጀት፤ተግባርና ኃላፊነት፣በስነ-ምግባርና የስጋት ቦታ ልየታና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩርም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።ስልጠናው የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬ ህይወት በለጠና ም/ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ዲቪዚዮን ሀላፊ ተሰጥቷል ።

ስልጠናው በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።