የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት ድጋፍና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ

የቢሮው የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ ሪፖርት በመገምገም በማኔጅመንት ኮሚቴ የተቀመጡ የቀጣይ አቅጣጫዎችን የጋራ አደረገ።

ታህሳስ 08/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት በ11ዱም ክፍለ ከተሞችና በተመረጡ 11 ወረዳዎች ላይ በ3 ቡድኖች የተደረገው ድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ ሪፖርት ገምግሟል።

የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት የድጋፍና ክትትል ሪፖርት በሶስት ቡድን ተከፍሎ የቀረበ ሲሆን በድጋፍና ክትትል የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር አብራርተዋል።

ሁሉም ክ/ከተሞችና በታዩ ወረዳዎች ላይ በዕቅድ እየመሩ መስራታቸው፤ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የተገልጋዮች ምዝገባና አስተያየት መስጫ ስርዓት መዘርጋቱ እና የቀረቡት ቅሬታዎች ሂደቱን ጠብቀው መፍታታቸው እንዲሁም ወንጀል ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች፤ በቅንጅት ስራዎችን ለመምራት የሚደረግ ጥረት፤ ለተለያዩ አደረጃጀቶች የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በጥንካሬ የቀረቡ ሲሆን የመረጃ አያያዝ ክፍተት፣ ምርጥ ፈጻሚ በመስፈርቱ መሰረት የመለየት፤ ስራዎችን በስታንዳርድ የመምራት፤የግብዓትና የሰው ሃይል እጥረት እንደ ችግር ተጠቅሷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ም/ል የቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ እንዳሉት የተገኙ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን በአስቸኳይ በመሙላት የዘርፉን አፈፃፀም ማላቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አቶ ተስፋዬ አክለውም በሱፐርቪዥን የተገኙ ግኝቶችን በወጉ ቆጥረን በመያዝና ራሱን የቻለ እቅድ በማዘጋጀት መልካም ስራዎችን ማላቅና ጉድለቶች ማረም ከያንዳንዱ ሰራተኛ የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ያሳሰቡ ሲሆን በቢሮው ማኔጅመንት ኮሚቴ የተቀመጡ አቅጣጫዎችም ለአስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች ማብራሪያ በመስጠት ሀላፊነታቸው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ም/ል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደንድር፣የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች የወረዳ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።