በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 08/2017ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህግ ቡድን ለቢሮው ሰራተኞች የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ በቃሉ ከበደና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የጥናትና ምርምር ባለሙያ አቶ ደምሰው ሽፈራው ናቸው።
አቶ በቃሉ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ይህ ስልጠና ትኩረት የሚያደርገው የህግ ማዕቀፎች ላይ ሲሆን ለቅጥር የሚያበቁመስፈርቶች፣የሙከራ ጊዜ፣የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ፣የስራ አፈጻጸም ምዘና አሰጣጥ የመንግስት ሰራተኞች ግዴታንና ሌሎች በወጡ አዋጆች ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ በቃሉ አክለውም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የመንግስት ስራተኞች መብትና
ግዴታቸውን፣የተለያዩ አዋጆች፣መመሪያዎች ደንቦች ፖሊሲዎች እንዲያውቁና ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው ብለዋል።
የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም መንግስታዊ አስተዳደር ምንነት፣ፅንሰ ሀሳብናመርሆዎች ዙሪያ አቶ ደምሰው ሽፈራው ስልጠና ሰጥተዋል።