የቀጠለ ዜና

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቀጠለ ዜና

ለሰላም ሰራዊት ነባር የብሎክ አመራሮች መሠጠት የተጀመረው የንድፈ ሀሳብና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና ዛሬም ቀጥሏል።

ታህሳስ 8 2017 (አዲስ አበባ )

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮችበንድፈ ሀሳብና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና በትላንትናው ዕለት የማስጀመሪያ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን ስልጠናው በዛሬው ዕለትም በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል።

የስልጠናው አላማ የሰላም ሰራዊቱን በማነቃቃት አቅሙን ክህሎቱን ውህደቱን ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።

በዛሬው ውሎ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት የሰላም ዋጋው ውድና በምንም የማይተመን መሆኑን ገልፀዋል።

የከተማዋን ህዝብ ሰላም፣ ልማትና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በንቃት በመጠበቅ፤የሰላም ሰራዊቱ ሌት በቁር ቀን በሀሩር በትጋትና በብቃት የተሰጣ

ቸውን የሰላም ተልዕኮ ይገናኛሉ ሲሉ የተናገሩት ሲሆን ሀላፊው አክለውም የከተማው ህዝብ ሰላም ወዳድ በመሆኑ ከሰላም ሰራዊትና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ስለሆነ ሊመሰገን ይገባዋል ሲሉ ተደምጠዋል ።

የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ በበኩላቸው ስልጠናው ግንዛቤን ለማሳደግ፤ ለማነቃቃትና በውህደት ለመስራት ህጋዊ አሰራርን ግልጽ ለማድረግ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ባህሩ አክለውም ሰላሟ የተረጋገጠ፣

ልማቷም የተፋጠነ፣አንድነቷ የፀና የዲፕሎማሲ ከተማን ለመጠበቅቁርጠኛ ለሆነው የሰላም ሰራዊት ድጋፍና ክትትል ከማድረግ በተጨማሪ በስልጠና በንድፈ ሀሳብና በተግባር ክህሎቱን እናሳድጋለን ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ፣የክፍለ ከተማው የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ፣የክፍለ ከተማው የሰላም ሰራዊት አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

ስልጠናው በቀጣይም ቀናት ቀጥሎ ሲውል የመስክ ተግባራዊ ልምምድ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል