የቀጠለ ዜና
የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የክ/ከተማውን ብሎም የከተማውን ሰላም እያስጠበቀ መሆኑ ተገለፀ።
ታህሳስ 09/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )
*****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለነባር የሰላም ሰራዊት አባላትና ለብሎክ አመራሮች የማነቃቂያ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፣ የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ጂሬኛ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘውን ጨምሮ የፀጥታ አካላት ፣ የከተማና የክ/ከተማ ባለሞያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በስልጠናውን ተሳትፈዋል ።
ስልጠናው በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ፣ አሰራር ስልጣንና ሀላፊነት ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 140/2014 እንዲሁም በወንጀል መከላከል ፣ በስነ-ምግባር ፣ በመረጃ ልውውጥ ፣ በስጋት ቦታ ልየታና የችግር አፈታት ስርዓቱ እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ለ3 ተከታታይ ቀናት ለሰላም ሰራዊቱ የመስክ ስልጠና እንሚሰጥ ተገልጿል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የሰላም ሰራዊቱ በከተማው እየሰራቸው በሚገኘው ሰላምን የማስጠበቅ ስራ የሌቦችና ወንጀለኞች ራስ ምታት እንደሆነ ጠቅሰው ስልጠናው የሰላም ሰራዊቱ ያለውን አቅም የሚያጎለብትበት መሆኑንና የሰላም ሰራዊቱ የስልጠና መልስ ያገኘውን ዕውቀት ለሌሎች ማካፈል እንዲሁም አካባቢውን በትኩረት በመጠበቅ የተገኘውን ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በስልጠናው ለሰላም ሰራዊቱ ወንጀል ከመፈጠሩ በፊት እና ከተፈጠረ በሁዋላ በምን መልኩ መከላከል እንደሚገባ በስፋት መቆረቡንና ይህም ለሰላም ሰራዊቱ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ምንም እንኳም ከተማዋ ሰላም የሰፈነባት ብትሆንም ጠላት ሁሌም ሰላሙን ለማደፍረስ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የከተማውን ሰላም በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ጂሬኛ በክ/ከተማው የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት በሰራው ስራ የክ/ከተማው ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀው ስልጠናው የሰላም ሰራዊቱን የሚያነቃቃ መሆኑን በማንሳት የሰላም ሰራዊቱ የመጣውን ሰላም በዘላዊነት ለማስቀጠል በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።