የሀይማኖት አባቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሀይማኖት አባቶች ትልቅ ሚና አላቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ
ታህሳስ 11/ 2017 (አዲስ አበባ )
**
ሀላፊው ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታና የሀይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ "አብሮነት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፣ከፊታችን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበር በተመለከተና እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ በጋራ መክረዋል።
በስልጠናውና ምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ ኢትዮጵያዊን እንደ እድል ሆኖ አማኝ ናቸዉ
ከሚባሉት ሀገራት ውስጥ አንዷ ስትሆን ህዝቦቿ በመከባበር፣በአንድነትና በፍቅር አንድ እንድትሆን ለማድረግ ብዙ መስዋዕትነት እንደተከፈለበት በመግለጽ ይህን ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን አንድነት አጽንቶ ማቆየት ይጠበቅብናል ብለዋል ።
የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ ኤልያስ ቀጄላ የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ አብሮነትና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ሁሉ በመተባበር ውስጥ ሰላም አለ ከሁከትና ከጦርነት አለም በመውጣት መከባበር፣ለሰላም መተባበርና የሀገርንም ሰላም ማስጠበቅ ከሰነዱ ጠቅሰዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊው አቶ ተስፋዬ ጫኔ እንደተናገሩት አብዛኛውን የአለም ህዝብ ሊሚያስማማው የሚችል ነገር ቢሮር አንዱ ሰላም መሆኑን ገልፀዉ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋ ገጥ አኳያ የሀይማኖት አባቶች ሚና ትልቅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሰላም ለሀገር ግንባታ ወሳኝነት እንዳለውም በመጠቆም የውሸት ትርክት በመንዛት
ትውልድን ከትውልድ የሚያጋጩ በርካታ ግለሰቦች ቢኖሩም ከብዙሃኑ ጥቂቶቹ ለሰላም መስፈን እንደሚሰሩ ይታወቃል ብለዋል።
የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአሁኑ ትውልድ ላይ በሚሰጠው የአስተምህሮ ስለሆነ ለዘላቂ ሰላማችን በጋራ መሥራት ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ ከፊታችን የሚከበረው የጥምቀትና የከተራ በዓልም ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሃይማኖት አባቶች ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።