የቀጠለ ዜና
"ወቅቱን የዋጀ አርበኝነት ለሰላም ግንባታ ያለው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 11 /2017 (አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታና የሀይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ" ወቅቱን የዋጀ አርበኝነት ለሰላም ግንባታ ያለው ሚና" በሚል ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ በመገኝት መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ሀላፊ እንዳሉት ያለፈን ትርክት በማንሳት ከሏላ የነበረን ነገር ብቻ በመገንዘብና ባለመረዳት ውስጥ እንደ ሀገር እውነታን ባለማወቅ አሁን ላይ እዚም እዛም የሚፈጠሩ ጸቦች አንዱ መገለጫዎቹ ሲሆኑ እንዳንግባባ እንዳንዋደድና ልዩነቶች እንዲፈጠሩም ምክንያት ሆነዋል ብለዋል።
ስለዚህ ትላንት የነበረን ኢትዮጵያን አሻግረን በማየት የወደፊት እይታንም በማስተካከል ሀገርን የማስቀጠል ተግባር ላይ በመሳተፍ ያለችና የምትኖር ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን ያቀረቡት ወ/ሮ አዲስ አለም ዘነበ የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ ከነጠላ ትርክት ወጥቶ ታላቋን ኢትዮጵያ የዋጀ አንድነት በማምጣት በሚያግባባ መልኩ በማንነቷ የማትደራደር አገርና አሸናፊ የሆነ ህዝብ ባለቤት መሆኗን፣የተረዳ ሀገሩን የሚወድ የዘመኑ አርበኛ መሆን እንደሚገባአብራርተዋል።