ቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ5ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ ።
ቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ5ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ ።
ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የዘርፉ አስተባባሪዎች፣ቡድንመሪዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ5ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።
የአምስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክ/ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች የቀረበ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት በ 5 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች፣ በዝግጅት ምዕራፍ ዋና ዋና ተግባራት፣ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር አብራርተዋል።
የህበረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ፣የንቅናቄ መድረክ መፍጠር፣ የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑ በማድረግ እና ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በአላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ማድረጋቸዉ ከጠንካራ ጎኖች ተጠቃሽ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮች ውስጥ ደግሞ የሰው ሃይልና የግብዓት እጥረት መሆኑ ተጠቅሰዋል።
መድረኩን የመሩት የዘርፉ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚዴክሳ ከበደ እንደተናገሩት የፀጥታ ስራ በቀን 8 ሰአት ብቻ ሰዓት ጠብቆ አቴንዳስ በመፍረም ብቻ የሚሰራ ስራ ስላልሆነ ሁላችንም ሃላፊነታችንን በፍቅርና በታማኝነት በመወጣት የከተማችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።