የፀጥታ ግብረ-ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረገ።
የፀጥታ ግብረ-ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረገ።
ታህሳስ 11(2017)፦
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር የፀጥታ ግብረ-ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረገ።
በውይይቱ ላይ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የፖሊስ ኃላፊውች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ላይ በቅንጅታዊ የፀጥታ አሰራር፤ ወቅቱን በመረዳት በቅድመ-መከላከል እንዲሁም የህብረተሰቡን ሰላምና የመንግስት ልማት በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሉ ምን ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦች ተነስተዋል።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ እንዳሉት የሰላምና ፀጥታ ስራችን እንዲረጋገጥ ህብረተሰቡንና የፀጥታ ኃይሉን በማቀናጀት፤ በተልኮ ብቃትና በአመለካከት ቁርጥኛ የሆነ የፀጥታ አመራር በመስጠት በንቃት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማትን፤ ብሔራዊና ሀይማኖታዊ በዓላትን በተጨማሪም በመዲናችን የሚደረጉ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ መድረኮችን ታሳቢ ያደረገ የፀጥታ ስራ ማከናወን ይገባል።
አቶ ባህሩ አክለውም አጎራባች ክፍለ ከተሞችን፤ የሸገር ሲቲን አስተዳደርን እንዲሁም የሰላም ሰራዊት በማቀናጀት ከተሰራ የልማትና የሰላም እንቅፋት የሆኑ ኃይሎችን አላማ በማክሸፍ ህገወጥነትን እንከላከላለን ሲሉ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮምሽነር ሽመልስ ሽፈራሁ በበኩላቸው አዲስ አበባ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ከተማ መሆኗን ጠቅሰው የሚመጥናትና የፀጥታ ጥበቃ ተግባራዊ ማድረግ ከእኛ ይጠበቃል ብለዋል።
ኮምሽነሩ አክለውም ከህዝብ ፍላጎትና ልማት በተቃራኒ የቆሙ የአፍራሽ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በማጤን የተጣለብንን ኃላፊነት በአግባቡ ልንወጣ ይገባል።
የውይይት መርሃ-ግብሩ የቀጣይ ስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።